News and Events
News
የጉልበት ህመም አስጨንቆዎታል?
ስለ ሜኒስከስ ጅማት (Meniscus Tear) ማወቅ ያለብዎት ነገሮች!
🦵 የሜኒስከስ ጅማት ጉዳት በስፖርት፣ በዳንስ ወይም በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ወቅት በድንገት በመጠምዘዝ የሚከሰት እጅግ የተለመደ የጉልበት ጉዳት ነው።
⚠️ ዋና ዋና ምልክቶች
🔹ከፍተኛ የጉልበት ህመም እና እብጠት
🔹ደረጃ ሲወጡ ወይም ሲወርዱ የሚሰማ ስቃይ
🔹ጉልበትን ማጠፍ ወይም መዘርጋት መቸገር (መቆለፍ)
🔹ጉልበት የመዛል ወይም የመክዳት ስሜት
🩺 መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?
ድንገተኛ የመጠምዘዝ ወይም የመዞር እንቅስቃሴዎች
ከመጠን በላይ የሆነ የሰውነት ክብደት
የጡንቻ ጥንካሬ ማነስ
ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የ cartilage መበላሸት
💊 የሕክምና አማራጮች
ባሉበት የጉዳት ደረጃ ላይ በመመስረት የሚከተሉት መፍትሄዎች ይሰጣሉ፡
✅ ፊዚዮቴራፒ: የጭን እና የዳሌ ጡንቻዎችን በማጠናከር ጫናን መቀነስ።
✅ እረፍትና በረዶ: ለህመም እና ለእብጠት ቅነሳ።
✅ የጉልበት ድጋፍ: ለተጨማሪ ጥንካሬ የሚደረግ ማሰሪያ።
✅ ቀዶ ሕክምና: በአርትሮስኮፒ (Arthroscopy) የታገዘ ዘመናዊ ህክምና።
🛡 ቅድመ ምርመራ ማድረግ የረጅም ጊዜ የአካል ጉዳትን ይከላከላል!
