News and Events

News

የዝንጀሮ ፈንጣጣ (MPox)

የዓለም ጤና ድርጅት የዝንጆሮ ፈንጣጣ አደገኛ የጤና ስጋት መሆኑን አወጀ

የዝንጀሮ ፈንጣጣ (MPox)

የዝንጀሮ ፈንጣጣ (MPox) የዓለም አቀፍ አሳሳቢ የህዝብ ጤና ደኅንነት ስጋት (PHEIC) እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ወሰኑ።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) እና በአፍሪካ የሥርጭት መጠኑ እየጨመረ መምጣቱን አሳውቀዋል። ከዚህ ባለፈ፣ የዝንጀሮ ፈንጣጣን የአፍሪካ ሲዲሲ የህብረተሰብ ጤና አህጉራዊ ደህንነት ስጋት እንደሆነ ገልጿል። በሌላ በኩል ፤ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ የተያዘ ሰው #አለመኖሩን የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ዛሬ አመልክቷል። በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት እና ሞያሌን ጨምሮ በሌሎች የመግቢያ ቦታ ላይ የቁጥጥርና ማጣራት ስራ እየተሰራ ነው።

በሽታው እስካሁን በ13 የአፍሪካ ሀገራት መከሰቱን እንዲሁም፣ 2,863 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው እና 517 ለህልፈት መዳረጋቸዉ መረጋገጡን የአፍሪካ በሽታዎች ጥናት ተቋም (African CDC) መረጃ ያሳያል።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ (MPox) ምልክቶች

  • ትኩሳት
  • ራስ ምታት
  • የእጢ (ንፍፊት) እብጠት
  • ሽፍታ
  • የጡንቻና የጀርባ ህመም
  • የቆዳ ቁስለት
  • አቅም ማጣት

በሽታው በቀጥታ ከሰው ወደ ሰው በንክኪ የሚተላለፍ እንደመሆኑ መጠን ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች የሚያሳይ ማንኛዉም ሰዉ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ሪፖርት ማድረግ ይኖርበታል እንዲሁም በቅርቡ በሽታው ወደ ተከሰተባቸው ሀገሮች የጉዞ ታሪክ ያለው ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው ወደ ሚገኝ ጤና ተቋም መሄድ ይኖርበታል !